ቀዳሚ ምኞቱ አራሽ መሆን ነበር። በወቅቱ መሬት ለባላባት እንጂ ላራሽ ስላልነበረ የቀለም ትምህርቱ ላይ ተጋ። ጊዜው ሲደርስ እርሻ ኮሌጅ ገብቶ ተመረቀ። ቤተሰብ ሲል፣ ሹመትና ዝውውር ሲል፣ አለቃ ሲጠምበት፣ ከተማ ለከተማ፣ ሚኒስቴር መ/ቤት ለሚኒስቴር መ/ቤት ሲንፏቀቅ፣ ከዚያ ለኮርስ ውጭ አገር፣ ልጅ…
በማር መጥተውባት፣ መሯት። ንቢት ንዴት አሳብዷት ቀፎዋን ጥላ ቱር አለች። በመስኮት ገብታ የአቶቡሱን ሾፌር አፍንጫው ላይ ነደፈችው። ሾፌር አፍንጫው ከምኔው ረዛዝሞ ዐይኑን ሲያጥበረብረው። መርዙ እ ንደ እልህ እንደ ቂም እንደ ጥላቻ እንደ አጋንንት ሳቅ ተሠራጭቶ እንደ እብድ እንደ ሰካራም ሲያደርገው።…
ከቤት ስወጣ እንደ ወትሮ እግሬን አፍታትቼ እመለሳለሁ ነበር እንጂ ይህንን ጒድ ጨርሶ አልጠበቅሁም። ከወዲያ ማዶ ጐረበቴ ቢስኪሌት ስትጋልብ አይቻት በሩቊ በአገሬ ወግ ሰላም አልኳት። አፃፋ እመልሳለሁ ብላ አንድ እጇን ለሰላምታ ስታነሳ የቢስኪሌቱ መሪ ወለም ብሎባት ይመስለኛል ፍንግል አለች። “እኔን! እኔን!”…
እንደ ዘመኑ ሰው ስልኩም ወሬኛ ወረተኛ ሆነ። የፈረንጅ ስልክ አገራችን ከመግባቱ በፊት ሰው ከወዲያ ወዲህ ተጠራርቶ መጫጯህ ወጉ ነበረ፦ “ወይፈኑ ከጊደሮችህ ጋር መጥቶ ይሆን? …ኡዉይ! … ጠበል ቅመሱ! ቡና ጠጡ! …ኡዉይ! … ወንዙን እንደ ተሻገራችሁ፣ ከጒብታው ላይ ኢየሱስ ይታያችኋል፤ በስተቀኝ…
ተስፋ መስጠቱን እንጂ እምነት መዋረድን እንደሚጨምር ብዙ ሰው አይገነዘብም። ውርደትን ቀምሶ ማሳለፍ ግን ውሎ ሲያድር የትዝታ ጠባሳ ትቶ ያልፋል።እምነት ስንል ሁለት መልክ አለው። በሰው የሚታመን አለ፤ በፈጣሪው የሚታመን አለ። ሁለቱም ይፈተናሉ። አንደኛው ይወድቃል፣ ሌላኛው ይፀናል። ይኸኛው ራሱን ለማስወደድ ወድቆ ይነሳል፤…
የዛሬዪቱ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ሰሞኑን የአቶ ስብሃት ነጋ ፎቶግራፍ በማኅበራዊ ሚድያ ተለቅቆ መነጋገሪያ ሆኗል።ፎቶአቸው እውነተኛ ማንነታችንን ያሳየን ይሆን? የፍትህ አምላክና የሕግ የበላይነት ጨርሶ እንዳልጠፉ ያስታውሰን ይሆን? ሰዎች ስንባል ከንቱነት የሚያጅበን ፍጡራን ነን።የህወሓት መሥራች አቶ ስብሃት እርጅናቸው በዚህ ይቋጫል ብሎ ያሰበ…
ሰው ከሞላ ጎደል የግንኙነቶቹ ውጤት ነው። ከወላጅ ቤት ትምህርት ቤት። ከደደቢት ከአሲምባ ምንሊክ ቤት። ከዳንስ ቤት ጸሎት ቤት። ከእሥር ቤት ፍርድ ቤት፤ ወደ ስደት ወደ አገር ቤት። የውጣ ውረዱ ተፅእኖ ቀላል አይደለም። መንገዱ ረጂም ዘወርዋራ ነው። ለያንዳንዱ ተሸክሞት የሚዞረው ኮሮጆ…
መስቀል እና ሠላጢን እንዴትና መቸ በማን እንደ ተጋጠሙ እቅጩን ማወቅ ያዳግታል። ሁለቱ የሚያበስሩት ፍልስፍና ግን የተድበሰበሰ ነገር የለውም። ወይ ሰላም ወይ ፀብ። ሰላም እና ፀብ። በሰላም ከመጣ አሳልመው፤ በፀብ ከመጣ ጎኑን ወግተህ ጣለው… ከጅምሩ የጠበኛና የጠርጣራ ሰው ሥራ ይመስላል፤ ጨርሶ…
መሪነት፣ የነገሮችን አካሄድና ፍጻሜ ከጅምሩ ለተለሙ ነው። መሪነት፣ ዐይናቸውን ከግባቸው ላይ ሳያነሡ በየእርከኑ ሁኔታን ለሚያቃኑ ነው። መሪነት፣ ምሥጋናን ለሚጋሩ ነው። መሪነት፣ ውርደት ውርደቱን ማንም እንደማይጋራቸው ለተገነዘቡ ነው። የመሪዎች አበሳ የሚጀምረው ዓላማቸውን ግልጽ ሳያደርጉ ሲቀር፣ ዓላማቸውን እንደየሁኔታው ደጋግመው ሳያጠሩ ሲቀር፣ ተቀናቃኞች…
ወደ አንድ መንደር መጣ። ከፊት ለፊቱ የሚታየውን ቤት ሄዶ አንኳኳ። ደጋግሞ አንኳኳ፤ የሰውም የውሻም ድምጽ አልተሰማም። አልከፈቱለትም። አለፍ ብሎ ሌላ ደጅ አንኳኳ። ማ ልበል? አሉ። ማ ልበል? ብለው ወሬአቸውን ቀጠሉ እንጂ ተነሥተው አልከፈቱለትም። ወረድ ብሎ አንኳኳ። ሲከፍቱለት ተገትሮ ቆሟል። ቊመናውን…