ጋዜጠኛው ፓሪስ ላይ ኮብልሏል።

ጋዜጠኛው ፓሪስ ላይ ኮብልሏል።

በፓሪስ ኦሊምፒክ ከኢትዮጵያ ልዑክ ጋር የፕሬስ አታሼ ሆኖ የተጓዘው የዋልታ ቲቪ ጋዜጠኛ ሀብታሙ ገደቤ ወደ ሀገር ቤት አለመመለሱ ታውቋል። ጋዜጠኛው ፓሪስ ላይ መኮብለሉና ለቤተሰቦቹም ኢትዮጵያ እንደማይመለስ መናገሩን የኢትዮጵያ ኦብዘርቨር ምንጮች ገልጸዋል። ወድ ኢትዮጵያ ለተመለሱ የልዑክ አባላትም ለቤተሰቡ የሚሰጥ እቃዎችን መላኩን ጨምረው ተናግረዋል። ሀብታሙ ገደቤ ከቅርብ ግዜያት ወዲህ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ የመድረክ ፕሮግራሞችና የውድድር መድረኮችን በአስተዋዋቂነትም በመስራት ይታወቃል። በፓሪስ ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ ፕሬስ አታሼ የሚል ባጅ የወሰደ ቢሆንም በወቅቱ ምንም አይነት የፕሬስ አታሼነት አገልግሎት ሲሰጥ አልተገኘም።

የውሀ ዋና ተወዳዳሪዋ ሊና አለማየሁ አሰልጣኝ የነበረው አንተነህ ጎበዜም እንደዚሁ መኮብለሉ ተሰምቷል። ሊና ለግማሽ ፍፃሜ ብቃት ሀምሌ 27 በተካሄደው የ50 ሜትር ነፃ ቀዘፋ ውድድሯን ካከናወነች በኋላ አሰልጣኙ በዚሁ ቀን ፈረንሳይን ለቅቆ ወደ ሌላ የአውሮፓ አገር መሄዱ ተነግሯል።

Share this post