ዕድሜ ጠገብ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅርሶች ወደ ፈረንሳይ እንዴት ተወሰዱ?

ዕድሜ ጠገብ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅርሶች ወደ ፈረንሳይ እንዴት ተወሰዱ?

ፈረንሳዊው ማርሴል ግሪዩል ከ1928 እስከ 1929 እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት 16 በግእዝ የተጻፉ ጥንታውያን የብራና መዛግብት ይዞ ወደ ሀገሩ ተመልሷል።እንዲሁም የዳካር ጂቡቲ ተልዕኮ (La mission Dakar-Djibouti) ተብሎ የሚታወቀው ከ1931-1933 የተደረገ ሌላ ዘመቻ ይሄው ማርሴል ግሪዩል ከሌሎች አባላት ጋር በመሆን በግእዝና በአማርኛ የተጻፉ 333 መዛግብት ፣ የሚጠቀለሉ የጽሑፍና የኪነ ጥበብ ውጤቶች ሰብስቦ ወስዷል። መዛግብቱ ሃይማኖታዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፍቶች ፣ አጋንንትን የሚያሳድዱ ፀሎቶች፣ የምትሃት አሠራር ፣ ባህላዊ ህክምና፣ አልባሳት፣ ታሪካዊ ጽሑፎች ያካተቱ ናቸው። የዳካር ጂቡቲ የተልዕኮ ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ ያደረገው ጉዞ ወደ ሌሎች 14 የአፍሪካ ሀገራት ያደረገው ጉዞ አካል ሲሆን ስለአህጉሪቱ ባህልና እሴቶች ለማጥናት በሚል ሰበብ በሺህ የሚቆጠሩ የባሕል ዕቃዎችን ለመዝረፍ መንገድ ከፍቷል። አገራቱ ከኢትዮጵያ በስተቀር የፈረንሳይና የሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ቀኝ ግዛት የነበሩ ናቸው።ከተልዕኮ ቡድን አንዱ የነበረው ሚሼል ሌሪስ 1934 ላይ ባሳተመው L’Afrique Fantôme በተባለው መጽሐፉ፤ ሳይንሳዊ ጥናት በሚል ሰበብ የቅርስ ዝርፊያ ላይ በመካፈሉ የተሰማውን ጸጸት ገልጿል።

እነዚህ በርካታ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች ከኢትዮጵያ እንዴት እንደወጡ ዛሬ ዛሬ ብዙ ጥያቄዎች አሉ።የ’ዳካር ጂቡቲ ተልዕኮ’ ጎንዳር ከተማና ባካባቢው ለአምስት ወራት በመቆየት የቤተ ክርስቲያን ሥዕሎችና የብራና መጻሕፍት በተለያየ መንገድ አሰባስበዋል።

ሰሞኑን በፓሪስ የሚገኘው Le musée du quai Branly ተብሎ የሚጠራው ሙዚየም እነዚህ ቅርሶች እንዴት እንደተሰበሰቡ የሚገልፅ ኤግዚቢሽን እያሳየ ነው። ከኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ቤኒን፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ ኢትዮጵያና ጅቡቲ የተውጣጡ ምሁራንና ባለሙያዎች ከሙዚየሙ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ወደ ስፍራው በመመለስ የተወሰኑ ዕቃዎች እንዴት እንደወጡ ጥርት ያለ መረጃ ለለማግኘት ተሳትፈዋል።ከኢትዮጵያ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር፣ ሲሳይ ሳህሌ በየነ በፕሮጀክቱ ከተሳተፉት መካከል አንዱ ናቸው ።ኤግዚቢሽኑ ከሚያነሳቸው ጉዳዮች መካከል፤ ቡድኑ ቅርሶቹን ለመውሰድ ክፍያ ፈፅመዋልን? ከሆነስ ለማን? አንድ ካሃን የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በራሱ ውሳኔ መሸጥ ይችላልን? በትርጉም ሥራ ቡድኑን የረዱት ሰዎች እነማን ናቸው? 

ኤግዚቢሽኑ እስከ መስከረም 14 ቀን 2025 ዓ.ም. ድረስ ይቆያል።

Share this post

Post Comment