ዩክሬን እና አሜሪካ በማዕድን ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የዩክሬን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦልጋ ስቴፋኒሺና ተናግረዋል።
የዩክሬን የዜና ድረ ገጽ ዩክሬንስካ ፕራቭዳ “ሰነዱን የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪ ሲቢጋ እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እንደሚፈርሙት” ገልፆል።
ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ቀደም ሲል ለዩክሬንን ላደረገችው እርዳታ በምላሹ የዩክሬንን ማዕድናት ለመጠቀም እድል እንዲሰጣት ሲጠይቁ ነበር። ዩክሬን በበኵሏ በቀጣይ የደህንነት ዋስትናዎች እንዲሠጣት ጠይቃለች።
አሜሪካ ለዩክሬን የሰጠችው ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያ እርዳታ 500 ቢሊዮን ዶላር ገደማ መሆኑን የተናገሩት ትራምፕ፤ አገራቸው የዚህን ገንዘብ ያህል የሆነ የዩክሬን ማዕድን እንድታገኝ እንደምትፈልግ ገልጸዋል።
ከዓለም ብርቅዬ ማዕድናትን ውስጥ 5 % ገደማ በዩክሬን እንደሚገኙ ይገመታል።ይህ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ ለመሥራት የሚያገለግል የተረጋገጠ 19 ሚሊዮን ቶን የግራፋይት ክምችትን ያጠቃልላል። በተጨማሪም ዩክሬን ለባትሪዎች ቁልፍ ግብዓት የሆነው ሊቲየም፣ ከጠቅላላው የአውሮፓ ክምችት መካከል አንድ ሦስተኛው ይገኝባታል።