የትራምፕ የበዓለ ሲመት ንግግር፤ ቀይ ምንጣፍ፤ ስጋት

የትራምፕ የበዓለ ሲመት ንግግር፤ ቀይ ምንጣፍ፤ ስጋት

“ሕግ መንግሥቱን ለማስጠበቅ፣ ለመመከት እና ለመከላከል አቅሜ በፈቀደው ሁሉ ኃላፊነቴን በታማኝነት ለመወጣት ቃል እገባለሁ። ለዚህም ፈጣሪ ይርዳኝ!” በማለት ቃለ መሐላቸውን የፈፀሙት 47ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገፃቸው ፈገግታ አልባ ነበር። ዋሽንግተን ውስጥ በሚገኘው በምክር ቤቱ ህንጻ “ካፒቶል ሮቶንድ” አዳራሽ በተከናወነው ሥነ ሥርዐት ላይ ልክ ኮስተር ብለው እንደተነሱት ኦፊሴላዊ ፎቶ ሁሉ ፊታቸው እንደጨፈገገ ነበር። ወደ መድረኩ ወጥተው ንግግራቸውን ሲጀምሩ ብቻ ነው ፊታቸው ትንሽ ፈታ ያለውና “የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን” መጀመሩን ያበሰሩት።”ከዚህ ቅጽበት ጀምሮ የአሜሪካ ውድቀት አብቅቷል” የሚል ንግግር ከተሰናባቹና ለግማሽ ምዕተ ዓመት አገራቸውን ያገለገሉት ጆ ባይደን በተቀመጡበት አሰምተዋል።

ከስምንት ዓመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመረጡ እንዳደረጉት ንግግር ሁሉ ለአሜሪካ ሕዝብ “ጥንካሬን” የማስመለስ አላማቸውን ገልፀዋል።የትናንቱ ንግግር ከዚህ ቀደሙ አጠር ያለ ግን ጠንከር ያለ ሲሆን፤ ይህም የሀገራቸው ድንበርና በሀገሪቱ በህገ ወጥ መንገድ የሚገኙ ዜጎችን በብዛት ማባረር፣ አሜሪካ በሌሎች አገሮች ላይ “የሚኖራትን ዘላቂ የበላይነት” የሚገልፅ ነበር። “አሜሪካ የወደቀበችበት የአራት ረጅም ዓመታት መጋረጃ ይዘጋና አዲስ የአሜሪካ ጥንካሬ እና የብልጽግና ቀን እንጀምራለን” ብለዋል። በሜክሲኮ ድንበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሚደነግጉ ሲናገሩ ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተደርጐላቸዋል። ትራምፕ ኃይል ለማመንጨት የሚደረግ ቁፋሮ እንደሚቀጥል (« Drill, baby, drill ») በማለት፣ ገልፍ ኦፍ ሜክሲኮ ገልፍ ኦፍ አሜሪካ እንደሚባል (በዚያች ቅጽበት ሂላሪ ክሊንተን በማሾፍ አይነት ሳቅ አፍኖ ሲታገላቸው ይታያሉ) ና ፓናማ ካናልን አሜሪካ እንደምትወስድ ፤ ግዛቷንም እስከማርስ ድረስ እንደምታሰፋ ተናግረዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ባለው ከባድ ብርድ ምክንያት የተነሳ ሥነ ሥርዐቱ ምክር ቤት ህንጻ “ካፒቶል ሮቶንድ” ስለተደረገ በርካታ ሰው ተጨናንቆ ነበር። ይህ ሥነ ሥርዓት ሮናልድ ሬገን በ1985 ዓ/ም ካደረጉት የቤት ውስጥ በአለ ሲመት ወዲህ የመጀመርያው ነው። በቃለ መሐላ ሥነ ስርዐት ላይ የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶች ጆርጅ ቡሽ፣ ቢል ክሊንተንና ባራክ ኦባማ ሲገኙ እንደ አሌክሳንድሪያ ኦካሲዮ ኮርቴዝ ያሉ አንዳንድ ዲሞክራሲያዊ አባላት ለመታደም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።የቴስላና የኤክስ ባለቤት ኢላን መስክ፣ የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ፣ የሜታው ማርክ ዘከርበርግ እና የቲክቶክ የሥራ አስፈጻሚ ሹ ዚ ቼውም ፊት ለፊት ተቀምጠው ነበር። የትዳር አጋሮቻቸውም በገዥዎችና በኮንግረስ አባላት ሊያዝ የሚገባውን ወንበር ተቀምጠውበታል። በአሜሪካ የፕሬዚዳንት በዓለ ሲመት መሪዎችን መጋበዝ ያልተለመደ አሠራር ቢሆንም የጣሊያን ቀኝ አክራሪ ፓርቲና ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ መሎኒ፣ የአርጀንቲናው ፕሬዝደንት ሃቪየር ሚሌና የቻይና ምክትል ፕሬዝደንት ሃን ዤንግ፣ በዝግጅቱ ላይ ታድመዋል።

ዶናልድ ትራምፕ በግግራቸው በሐማስ ተይዘው የነበሩት የእስራኤል ታጋቾችን በማስለቀቅ የነበራችውን ሚና ከገለፁ በኋላ ለሰላም የቆሙና አገሪቱን አንድ ለማድረግ የቆሙ መሆናቸውን ገልፀዋል። ትራምፕ “አንድነት” የሚሉት በራሳቸው አተያይ መሆኑ እንዳለ ሆኖ። የ”አሜሪካንን ውድቀት” በተጋነነ መልኩ ማቅረብ፣ የፖለቲካ ባለንጣዎቻቸው ላይ ማላገጥና ማሾፍ፣መውቀስ እንዲሁም ሀገራዊ አንድነት ለማምጣት የገቡትን ቃል የሚፃረር ሃይል የተቀላቀበት ንግግር ማድረግ። ፕሮግራሙ ላይ የነበረው የፀሎትና የስብከት ሥነሦርዐት አንድነትን አያንፀባርቅም ነበር። ፓስተሮችና የአይሁድ ካህናት ለMAGA ተከታዮች የሚመች ፀሎትና የትራምፕን ጠላቶቹን የሚያወግዝ መልዕክት ሲያስተላልፉ በፕሮግራሙ ላይ ቡራኬ ያቀርባሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩት የሚሺጋን ኢማም በመጨረሻው ሰዓት ላይ እንዳይሳተፉ ተደርገዋል።በምርቃት ላይ ንግግር ያደረጉት የሚኒሶታ ዴሞክራቲክ ሴናተር፥ ኤሚ ክሎቢሻር ይህ ሥነ ሥርዓት እዚህ በካፒቶል የሚከናወንበት ምክንያት አለ በማለት ተናግረዋል።”በሌሎች አገሮች፣ በፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግሥቶች፣ በቢሮ ሕንፃ ውስጥ ሊሆን ይችላል እዚህ ግን የህዝቡ ቤት ተብሎ በሚወሰደው አዳራሽ ነው የሚደረገው።ይሄም የዴሞክራሲያችን መሰረት የሆነው የመቆጣጠር፣ ማመጣጠን (ሚዛን መጠበቅ) ሥርዓት እንዳይዘነጋ ተገቢ ማሳሰቢያ ነው” ብለዋል።”ሦሥቱ የመንግሥት አስተዳደር ቅርንጫፎች ለ250 ዓመታት ያህል በሕግ የበላይነት ላይ የተመሰረተው ታላቁ የአሜሪካ ዴሞክራሲያችን እንደ መሠረት ድንጋይ ሆኗል።” ሲሉም አክለዋል።

ከታላቅ ብርድ ጋር፥ በውጭ ያለው ድባብ ከውስጡ የተለየ ነበር። በሺዎች የሚቆጠሩ ናሽናል ሞል ተብሎ በሚጠራው ከምክር ቤቱ ህንፃ ደጃፍ መስክ ላይ ተሰብስበው በስልካቸው በዓለ ሲመቱን ሲከታተሉ ነበር፡፡ ብዙዎቹ የ MAGA ኮፊያ አጥልቀው በአካባቢው ያሉ ካፌዎችንና ቡና ቤቶች ሞልተው ነበር ። ከቃለ መሐላቸው በኋላ ትራምፕ በዋሽንግተን ዲሲ ካፒታል አሬና በተባለው የስፖርት እና የመዝናኛ ስታዲየም በመሄድ እዚያው ለተሰበሰቡ ደጋፌዎቻቸው ንግግር አድርገዋል።

Share this post

5 thoughts on “የትራምፕ የበዓለ ሲመት ንግግር፤ ቀይ ምንጣፍ፤ ስጋት

  1. Trump is telling Americans that all those progressive ideas are false. When he claims that immigrants eat dogs and cats, few Americans believe him. However, this serves as a way of implying that many immigrants have unfamiliar or unusual customs—that they are not like ‘us.’ Unfortunately, many white people agree with this sentiment. By opposing equality between men and women, as well as the rights of LGBT people and transgender individuals, he appeals to the fabric of a nostalgic vision of a ‘golden age’ from the past—an era when the factory worker man was the breadwinner of the family and the woman stayed at home. However, this so-called golden age was also an era of racial segregation. The idea that Trump stands for the common people is a myth. His alignment with billionaires and millionaires is no accident—he works for their interests. Under his administration, they will continue to get richer. Trump distracts from this fact by placing the blame on immigrants.

    1. Americans have chosen a fascist lawless racist a liar and a bigot and they will pay for it dearly. It is the season for Trump, his family, and billionaires to rip the nation and the world of resources. It will also be a season for public protests and Trump using the levers of power to sic dogs and militia on citizens. The only way to stop fascists is to resist them.

  2. Teddy and Alem, you are right. Ethiopia should beware of Trump and stay as far away from him as it can.
    He is a very clever man. And he will be they first one to tell you that! That’s the problem.

  3. I can’t share exact numbers, but many Americans of Ethiopian origin voted for Trump. Why would they support a white nationalist who thrives on insulting and denigrating minority communities? I believe it’s largely due to social issues and the perception that their family values align more closely with Trump’s views. Ethiopians tend to be conservative, even by African standards. Trump’s discourse against transgender and LGBT people is a widely held view among Ethiopians.

Comments are closed.