የትራምፕ የበዓለ ሲመት ንግግር፤ ቀይ ምንጣፍ፤ ስጋት
“ሕግ መንግሥቱን ለማስጠበቅ፣ ለመመከት እና ለመከላከል አቅሜ በፈቀደው ሁሉ ኃላፊነቴን በታማኝነት ለመወጣት ቃል እገባለሁ። ለዚህም ፈጣሪ ይርዳኝ!” በማለት ቃለ መሐላቸውን የፈፀሙት 47ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገፃቸው ፈገግታ አልባ ነበር። ዋሽንግተን ውስጥ በሚገኘው በምክር ቤቱ ህንጻ “ካፒቶል ሮቶንድ” አዳራሽ…