እስከ ቅርብ አመታት ድረስ፥ የኢትዮጲያዊያን አመጋገብ፥ ጥሩ የሚባል ነበር። በሀገር ውስጥ ከሚመረቱ የምርት ውጤቶች የሚዘጋጁ የምግብ አይነቶች፥ ለሰውነት እና ለጤና ተስማሚ የሚባሉ ነበሩ። ለዚህም ነበር አገሪቷ በበአንዳንዶች ዘንድ Organic Ethiopia የምትባለው።አሁን ግን በሚያሳዝን ሁኔታ፥ በዘመናዊነት ስም የኢትዮጲያ ምግብ በተለይ በከተሞች አካባቢ፥ የምዕራባዊ ይዘት እንዲይዝ እየተደረገ ነው። የሀገሬው ምግቦች፥ ምዕራባዊ ለማድረግ መሞከር በጤና ላይ፥ ጐጂ ተፅዕኖ እንደሚፈጠር፥ ብዙ ማስረጃ ቢኖርም የኢትዮጲያ መንግስት፥ ለምዕራባውያን ምግብ አምራቾች በሩ ክፍት እንደሆነ እየነገራቸው ነው።
ፒዛ ሃት የተባለው የምግብ ድርጅት በአዲስ አበባ አራት ቅርንጫፎችን ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ ነው።በርገር ኪንግ እና ኬኤፍሲ አገሪቱ ውስጥ ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውም ተዘግቧል።ኮካ ኮላ፣ ፔፕሲ እና Red Bull ምርታቸውን እና አገልግሎታቸውን እያሳደጉ ነው። እነዚህ ስማቸው በአለማቀፍ ደረጃ የታወቀ በመሆኑ ትኩረት ቢስቡም የምግብ ይዘታቸው ተመሳሳይ የሆኑ፤ ዝቅተኛ የንጥረ ምግብ ይዘት ያላቸው ምግቦች (low nutritional value ) እና አለቅጥ ስኳር የበዛባቸው ምግቦች፤ የሚያዘጋጁ ምግብ ቤቶች እና መጠጥ ቤቶች በየአካባቢው አየተከፈቱ ነው።
መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጐች ከመጨመር ጋር ተያይዞ የሰውነት ውፍረት እና የስኳር በሺታም እንዲሁ እየጨመረ ነው። ይህ በመንግስት ጥረት ላይ ጥያቄን ያጭራል። መንግስት ኢኮኖሚውን እና የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ ሲል የውጭ ሀገራት የምግብ አምራቾች እንዲገቡ ጥረት ቢያደርግም በፉብሪካ ሂደት ያለፉ ምግቦች (processed foods) በጤና ላይ የሚፈጥሩትን አሉታዊ ተፅዕኖ እምብዛም ትኩረት የሰጠው አይመስልም። አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች የለስላሳ ማስታወቂያዎች መበርከት እያሳሰባቸው መጥቷል።
ሌሎች እንደሚሉት፥ በአትክልት፣ ጥራጥሬ እና ፍራፍሬ ላይ የተመረኮዘው የኢትዮጲያ ባህላዊ አመጋገብ አሁን፣ አሁን ወደ ከሱቅ በሚገዙ ምግቦች “store-bought alternatives” እየተቀየረ ነው።
የዘይት፣ ስብ፣ ስኳር እና የእንስሳት ውጤቶች ፍጆታ በጣም እየጨመረ ነው። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከዛሬ ከሁለት አመታት በፊት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በአገራችን ከሚከሰተው ሞት 52 በመቶ የሚሆኑት መንስኤያቸው ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በተለይም ከልብና ደም ስር ጋር የተያያዙ ህመሞች፣ ካንሰር፣ የስኳር በሽታ እና ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ህመሞች በከፍተኛ ደረጃ እየጨመሩና የህመም፣ የሞትና የአካል ጉዳት መንስኤ እየሆኑ መምጣታቸውን ሚኒስቱሩ ገልፇል። ከሁሉም በላይ ኢትዮጲያዊያን ከመጠን በላይ ክብደት ባይኖራቸውም እንኳ በተለይ ለስኳር በሽታ የተጋለጡ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ቁጥር ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ከፍተኛው መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር ከዚህ ቀደም ገልጽዋል፡፡ ማህበሩ የስኳር ህሙማን ቁጥር በፍጥነት እያደገ መምጣቱን እና ህሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሆኑን አብራርቷል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ኢትዮጲያ ኦብሰርቨር ካነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መካከል በሙያው አርክቴክት የሆነው አኪላስ አበራ እንዲህ ይላል። «ከአረብ ሃገራት በርካሽ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ ብዛት ያላቸው የምግብ ዓይነቶችን እና እንደ ኮካ ፣ሚሪንዳ የመሳሰሉ መጠጦች ጤና ላይ የሚያደርሱትን ችግር ብዙም ትኩረት ያደረገበት አልያም ደግሞ ግንዛቤ ያለ አይመስለኝም። አዲስ አበባ ውስጥ ከግዜ ወደ ግዜ ቁጥራቸው በርካታ ጤናማ የማይመስሉ የሆነ ሰዎችን እያየሁ ነው። አለቅጥ ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች አዘውትሮ መመገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የሚያበረታታ ባህል አለመኖር ዋነኛው የችግሩ አካል ነው።ሰዎችም ይህንን ጉዳይ አሳሳቢ አድርገው ስለማይመለከቱት በሚቀጥሉት ዓመታት የስኳር እና የደም ግፊት በሽታዎች በበርካቶች ላይ እንደሚጨምሩ እገምታለሁ ፡፡ »
ሌላ በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነው እና ስለ ምግብ በተደጋጋሚ የሚፅፈው ጋዜጠኛ ሳሙኤል ጌታቸው እንደሚለው «አሁን አሁን በብዙ አካባቢዎች በተለይም በትምህርት ቤት አካባቢ፣ ታዳጊዎችን ሱሰኛ የሚያደርጉ (fast food) ምግብ ቤቶች እየበረከቱ ነው። ለእንደዚህ አይነት የምግብ አይነቶች ግዙፍ እና እያደገ ያለ ገበያ አለ ፡፡ »
ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የለስላሳ መጠጥ ፍጆታ ምን ያህል ነው? ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች አንፃር፥ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት፥ የተጠናከረ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። ግን የኮካኮላ የኢትዮጲያ አክሲዮን ባለቤት ከሆኑት አንዱ ንጉሴ ሀይሉ ለኢትዮጲያ ኦብሰርቨር እንደተናገሩት፥ ለምሳሌ ከጐረቤቷ ሀገራችን ኬንያ አንፃር፥ የኮካ ፍጆታ አነስተኛ ነው። በአመት፥ 80 ሚሊዮን የፕላስቲክ ሣጥን (Crate) አልደረስንም። የኬንያ ከ100 ሚሊዮን አልፏል።ናይጀርያ፣ ግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ ከ 300 በላይ ናቸው።ዳሩ ግን፥ የአገሪቱ የለስላሳ መጠጦች ፍጆታ እየጨመረ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።
የለስላሳ መጠጥ ፋብሪካዎች ምርታቸውን ለማስተዋወቅ ግዙፍ መዋዕለ ንዋይ ያፈሳሉ።በኮቪድ አማካኝነት ብዙ እንቅስቃሴዎች ተቋርጠው በነበረት ሰዐት እንኳ፥የኮካኮላ ድርጅት ከዱቄት እርዳታ ጋር የለስላሳ ምርቶቹን ያድል ነበር። ይህ “በጐ ስራውን” በማህበራዊ ሚዲያዎች ሳይታክት ሲያስተዋወቅም ነበር። አንዳንዶቹ ማስታወቂያዎቹ ህፃናት እና የለጋ ዕድሜ አባላት ላይ ያተኮሩ ናቸው።በትምህርት ቤቶች እና ህፃናት በሚጫቱቸው ቦታዎች ሳይቀር ያለ ምንም ገደብ ያስተዋውቃሉ።
ይህን ማድረግ በአብዛኛዎቹ የአውሮፖ ሀገራት የተከለከለ ቢሆንም እንደ ኢትዮጲያ ባሉ ሀገራት ግን መንግስታት አይናቸውን ጨፍነዋል።በርካታ የአውሮፖ ሀገራት የዓለም የጤና ድርጅት ባቀረበው ምክር መሠረት ነው ፣ ከመጠን በላይ ውፍረት ለመዋጋት በስኳር ነክ መጠጦች ላይ ከፍተኛ ግብር ጥለዋል። በፈረንሳይ ዋናዎቹ የምግብ ምግብ አምራቾች ከመንግስት ጋር ቃል ኪዳን በመፈረም ተጨማሪ ስኳሮች ፣ የኢንዱስትሪ ቀለማትን ፣ saturated ቅባቶች ከመጨመር ታቅበዋል፡፡ ግን በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች አንዳንድ ብራንዶች አሁን በምዕራቡ ዓለም የተከለከሉ ቴክኒኮችን እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ይህ እንደ ኢትዮጲያ ያሉ ሀገራትን ብዙ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች።
ዋና ፎቶ: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኮካ ኮላ ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችተቀብለው ሲያነጋግሩ ተቀብለው ሲያነጋግሩ
How about the new jobs these new markets will create? May be as we diversify what we eat, the price of teff will decrease or may be these companies will get their supplies from local farmers ..etc. There are different ways of looking at this dev’t. I think its good that we will have this options. Not all pizza and burger is bad. You can go to Europe and have this same products made with healthy ingredients. You can also educate people to consume these products in moderation.
Good thinking, that is exactly how I see it. The problem is most of us have the tendency to reject things before even trying to understand the most basic elements of the things we have an opinion over.
This is untimely. Do you have any information about Malnutrition in out country which exceeds now 40%. overnutrition is not a problem for us now. let us fight first ”food for all” then we will worry for quality.
Some seem to inidcate that it is better to eat junk food than to go hungry. This is strange. But they don’t seem to see the wisdom of eating healty food. Because junk food could cost a lot countries like Ethiopia. The costs and complications of diabetes and related illness could overwhelm healthcare systems in Ethiopia. So please dont preach for junk food without having information.