ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርም በተወለዱ በ91 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “የሐሳብ ልዕልና ምልክት፤ የሰላማዊ ትግል አርአያ፣ ላመኑበት ነገር እስከ መጨረሻቸው ሞጋች፣ ላመኑበት እውነት ብቻ የሚቆሙት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እመኛለሁ “ ብለዋል፡፡

Share this post