ከልክ ያለፈም ትዕግስት፤ ከልክ ያለፈም የኃይል አጠቃቀም መንግስታዊ ባህሪዎች አይደሉም። አንዱ የመንፈሳዊ ሰው ሌላው የአፋኝ ቡድን ባህሪዎች ናቸው። ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጠው የሚለው መንፈሳዊ አስተምህሮት የመንግስት ባህሪ አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም። መንግስት ቀኝ ሲመታ መቺውን በሕግ ጥላስር አውሎ ተጠያቂ ያደርጋል እንጂ…