መልዕክተ ዘማሪ፣ ፉካሬ አዝማሪ August 3, 2020 | by Ethiopia Observer | ታሪኳ ጌታቸው እነዛ ቀደምቶች በላባቸው የሚያድሩ፣ ይታደሱ ነበር በህብረት ሲዘምሩ። መጣር፣ መጋር ሲያርድ፣ ሲተሳሰር ጉልበት፣ ማንጎራጎር ነው ደግ፤ ያነቃል ከድክመት፤ አዝማሪም ዘማች ነው፣ ሲገባ ጦርነት። ተማሪውም ሲጓዝ እፍኝ ቆሎ ቋጥሮ፣ እየዘገነ ነው ከግጥም ማሰሮ። ያለአልቃሹ እንባ አይወርድም ኃዘኑ፣ አይፈርስም ድንኳኑ።…