ባየር ራውንድአፕ የተባለው የጸረ ተባይ መድኃኒት ምርቱ ካንሰር ሊያሲዝ የሚችል ነው በሚል በቀረቡበት ክሶች ሳቢያ፣ እስከ 10.9 ቢልዮን ዶላር የመክፈል ግዴታ እንደተጣለበት የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ዘገበ።ክሶቹ በኩባንያው ላይ መመስረት የጀመሩት ሞንሳንቶ የተባለውን የእርሻ ኬሚካል አምራች ድርጅት ገዝቶ የራሱ አካል ካደረገ በኃላ እንደሆነ ጋዜጣው ዘግቧል ።ግዙፉ የጀርመን ኩባንያ በካሊፎርንያ የተመሠረቱበት፡ የመጀመርያዎቹ ክሶች ፍርድ ቤት ለከሳሾቹ፡ ያመዘኑ ሆነው ካገኛቸው በኃላ፣ በመላው አሜሪካ ወደ 125,000 ያህል ክሶች ተከትለው ቀርበውበታል።በዚህም፡ ባየር እልባት ላልተሠጣቸው ክሶች እስከ 9.6 ቢልዮን የሚደርስ ካሣ የሚከፍል ሲሆን፣ ወደፊት ሊቀርቡበት ለሚችሉ ማንኛውንም ዓይነት ክሶች ተጨማሪ 1.25 ቢልዮን ዶላር፡ መጠባበቂያ አድርጐ ያስቀምጣል።ከዚህ የካሳ ክፍያ እስከ 5 ቢልዮን የሚሆነውን በዚህ አመት፣ ቀጣዪን 5 ቢልዮን ደግሞ በ 2021 የሚከፍል ይሆናል።ክፍያው ኩባንያውን ለከፍተኛ የገንዘብ ወጪ የሚዳርግ ከመሆንም ባሻገር ዕዳዎቹን ከፍሎ የመጨረሱን ሂደት እንደሚያዘገየው ፋይናንሻል ታይምስ ገልጿል።በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት የተቀሩትን ክስ አቅራቢዎች “ጠቀም ባለው የካሣ ክፍያዎች” ማባበል እንደሚቻል እርግጠኛ መሆኑን የባየር ዋና ኃላፊ ዌርነር ቦውማን ለጋዜጣው ገልጿል።የካሣ ክፍያው ለረዥም ጊዜ ድርጅቱን፡ ሲያወዛግብ ለቆየው ጉዳይ መቛጫ እንደሚያገኝለት፣ እንዲሁም ወደፊት ሊመሠረቱ የሚችሉ ክሶች ከሚያስከትለው ቀላል የማይባል ኪሳራ እንደሚታደገው ኃላፊው ገልፀዎል።
ሞንሳንቶን በባየር ሥር የማጠቃቅልን ትልም ጠንሳሽ የሆነ ሚስተር ባውማን ፣በኩባንያው ላይ የሚመስርቱ ክሶች መበራከት ምክንያቱ፣ ጠቀም ያለ ድጐማ የሚደረግላቸው የአሜሪካ የጥብቅና ድርጅቶች የከፈቷቸው ዘመቻዎች እንደሆኑ ይናገራል።ባየር በ 2018 የአሜሪካውን የእህል ቢዝነስ ለመግዛት 63 ቢልዮን ያወጣ ሲሆን፣ ይህ የግዢ ውል የጀርመኑን ድርጅት የገበያ መሪነት ማማ ላይ ቢያስፈነጥረውም፣ በመጀመሪያ የሞንሳንቶ ምርት የነበረው ራውንድአፕ ግን ለፍርድ ቤት ጣጣ ዳርጐታል።